Gjør som tusenvis av andre bokelskere
Abonner på vårt nyhetsbrev og få rabatter og inspirasjon til din neste leseopplevelse.
Ved å abonnere godtar du vår personvernerklæring.Du kan når som helst melde deg av våre nyhetsbrev.
ይህ ስብስብ ሥራ ነው፡፡ አስከዛሬ ባጫጭር ልቦለዶችና በኖቭሌቶች ወግ የሠራኋቸው፣ የዝርው ሥነ ጽሑፍ ሥራዎቼ ስብስብ ነው፡፡ በዘመን፣ በጭብጥና በቅርጽ የተለያዩ በመሆናቸው ትውስባዊ ፍጥርታቸው የጋራ መለያቸው ነው፡፡ሕይወትና ሞት (1975)፣ የማለዳ ስንቅ (1980)፣ መቆያ (1980)፣ ቅንጣት (2008) የታተሙ ሲሆን፣ ባባደፋርና (1978) በነገ ተስፋ (2006) የጋራ ስብስብ ሥራዎች ውስጥ አንዳንድ ዘለላ ያጫጭር ልቦለድ ሥራዎቼ ይገኛሉ፡፡ እኒህ ቀዳሚ ሥራዎቼ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና በሌሎችም ዩኒቨርስቲዎች፣ ኮሌጆችና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላማርኛ ሥነ ጽሑፍ ማስተማሪያነት አጋዥ መጻሕፍት ሁነው ለረዥም ዘመናት አገልግለዋል፡፡ >፣ > እና >ን የመሳሰሉት ገጸ ባሕሪያት ካንባቢያን ሕሊና ውስጥ ስላልጠፉ ናፋቂያቸው ብዙ ነው፡፡ እናም ለትምህርት ማእከሎችም ሆነ ለመላው አንባብያን የይታተሙልን ጥያቄ ምላሽ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ፡፡ በስብስቦቹ ውስጥ የነበሩት ግጥሞችም እራሳቸውን ችለው በሌላ መድብል ለብቻቸው የሚታተሙ ይሆናሉ፡፡ደራሲው
ብያኔዎችና ክርክሮች ሁሉ በማህበራዊ የትስስር ገጾችና በአርእስተ ነገሮች ላይ ብቻ በተንጠለጠሉበት በዚህ ዘመን፣ በሶስት አህጉሮች መካከል እየተመላለሰ ቅይጥ የባህል ድንበሮችን ስላቆራረጠና ብዙ ቋንቋዎችን ስለተማረ አንድ ትንሽ ልጅ ታሪክ ማንበብ ማን ይፈልጋል? ይህ "ባዶነት" የተሰኘው መጽሐፍ ባለ ሦስት ክፍል እኔ በእንተእኔ ሲሆን፣ የመጀመሪያው ቅጽ በጨቅላ ሕፃንነቱ ከወላጅ እናቱ ስለተለያየና አባቱ ሲሞት በአክስቱ እጅ ለማደግ ስለተገደደ ልጅ የህይወት ጉዞ ይዳስሳል። ከባቱ ሞት በኋላ፣ እናቱ ድጋፍ መስጠት ባለመቻላቸው እና በየመን ከሚገኙት የአባቱ ቤተሰቦች ጋር ለመገናኘት የሚያስችል መንገድ ያጣው ይህ ልጅ፣ ከስምንት እስከ አሥራ አንድ ዓመቱ ባለው ጊዜ ውስጥ ብዙውን ጊዜ ቤት አልባ ሆኖ በጎዳናዎች ላይ ተንከራትቷል። ለመሆኑ ያለ ማንም ድጋፍ ያንን ከባድ ጊዜ እንዴት ሊያልፈው ቻለ? ዓድል በልጅነቱ ጥልቅ የአይሁድ፣ የእስልምና እና የክርስትና ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን ቀስሟል። እዚያው ኢትዮጵያ ውስጥ ወጣት ማርክሲስት በነበረበት ወቅት፣ በኮሚኒስት ፓርቲ የወጣቶች ንቅናቄ ውስጥ በመሳተፉ ለእስር ተዳርጎም ነበር፡፡ የአባቱን ቤተሰቦች ለመገናኘት ወደ የመን ከማቅናቱ በፊት ከገዳዮች ቡድን ጥይት ለጥቂት ነበር ያመለጠው። ልጁየተወለደውአዲስአበባ፣ኢትዮጵያ፣በድህነትውስጥከምትኖርየአሥራአምስትዓመትኢትዮጵያዊትእናትእናየሃምሳዓመትነጋዴ፣ከመካከለኛውምስራቅጡረታየወጣየእንግሊዝወታደር (የመኒሀድራሚ) ነበር።የዚያልጅታሪክይህነው።የጽናትእናየህልውናተምሳሌትየሆነውንታሪክእነሆ.የህይወት ታሪክዓድል ቤን-ሀርሀራ የተመሰከረለት ፕሮፌሽናል ፕሮጄክት ሥራ አስኪያጅ (PMP) ነው። በቢዝነስ አስተዳደር (MBA) የማስተርስ ዲግሪ፣ እና በቴክኖሎጂ/ኢንጅነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪ አለው። ላለፉት 30 ዓመታት በከፍተኛ ቴክኖሎጂ፣ በጤና እንክብካቤ፣ በምህንድስና፣ በዘይትና ጋዝ፣ በዓለም አቀፍ ረድኤት ሥራዎች ውስጥ ተሰማርቶ አገልግሏል። በመኖሪያ አካባቢው በሚገኝ ኮሌጅ ውስጥም የአስተዳደር ኮርሶችን አስተምሯል። የሁለት ሴት ልጆች ኩሩ አባት የሆነው አድል፣ ከሃያ በላይ ማራቶኖችን ሮጧል፡፡ እንደ አንድ ጎበዝ ተጓዥ የኪሊማንጃሮ ተራራን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ስፍር ቁጥር የሌላቸው የተራራ ጫፎችን በድል ወጥቷል።
Abonner på vårt nyhetsbrev og få rabatter og inspirasjon til din neste leseopplevelse.
Ved å abonnere godtar du vår personvernerklæring.